image
image
image
image
image

የፀጥታ አካላት ሐገራዊ ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሁልጊዜውም ዝግጁ መሆናቸው ተገለፀ::

ግንቦት 18, 2017
ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት እና ለሸገር ሲቲ ቡራዩ ክ/ከተማ መልካ ኖኖ የፀጥታ አካላት የአካባቢን 7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል:: በእለቱ ተገኝተው ለፀጥታ አካላት ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከዚህ ቀደም የከተማችንን ሰላምና ፀጥታን አስተማማኝ እንዳደረግነው 7ኛው ሃገራዊ ምርጫም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል:: የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው መላው የፀጥታ መዋቅራችን ሐገራዊ ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሁልጊዜውም ዝግጁ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት ከጸጥታ መዋቅሩና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የጸረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በስምሪት መርሐግብሩ ላይ ከላይ ከተጠቀሱ የስራ ሃላፊዎች በተጨማሪ ሌሎች ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በመጨረሻም ለስምሪቱ ስኬታማነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስፈላጊውን የቁሳቁስና የግብአት ድጋፍ ተደርጓል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች