image
image
image
image
image

በክፍለ ከተማው የሚገኙ ሁሉም የፀጥታ አካላት በወንጀል መከላከል ወቅት ያሳዩትን ውጤታማ ስራ በምርጫ ወቅትም ለመድገም እየሰሩ መሆናቸው ተገለፀ::

ግንቦት 10, 2017
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት መደበኛ የፀጥታ አካላትና አጋዥ ኃይል በተገኙበት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ የጋራ ውይይት አድርገዋል:: መድኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ሁሉ አቀፍ ሰላምና ደህንነት በማስፈን ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ የአጋዥ ጥበቃ አባላት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተናቧና ተቀናጅቶ መሠራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅና ዜጎች በነፃነት መብታቸውን እንዲጠቀሙ እና በምርጫው ወቅት የሚፈጠሩ የፀጥታ ስጋቶችን በቅንጅት በመቆጣጠርና የህዝቡን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ሁሉም የፀጥታ አካላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ መሆኑን ገልፀዋል። በክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ የወንጀል መከላከልና ማህበረሰብ አቀፍ ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ደገፉ በበኩላቸው ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ለሁሉንም የፀጥታ አካላትና አጋዥ ጥበቃ አባላት ተልዕኮና ስምሪት በመሰጠት የአካባቢን ሰላምና ደኅንነት መጠበቅና ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች