image
image
image
image
image

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊትና ፀጥታ መዋቅር ስምሪት ተሰጠ።

የካቲት 27, 2017
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የምሽት አንድ ማዕከል ስምሪት አዲስ ከተማ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፤ የሰላም ሰራዊት፤ ቅጥር ጥበቃዎች እና ሠላም ሠራዊት የፀጥታ አደረጃጀቶች በጥምር በተገኙበት የምሽት ስምሪት ተሰጥተዋል። በፕሮግራሙ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ የሰላምና ፀጥታ ስራ ወሰን የማይገድበውና በቅንጅት በመስራት ለአካባቢያችንን ብሎም የከተማችን ሰላም ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ስላለው መሰል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበው አሁን ያለንበት ወቅት ከፀጥታ አንፃር አስቸጋሪ ወቅት በመሆኑ በልዩ ትኩረት አከባቢን ፀጥታ ተግተን 7/24 መጠበቅ አለብን ብለዋል ሲሉ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው ከህብረተሱ ጋር በቅንጅት መስራት አካባቢያቸውን ከምን ጊዜም በላይ ትኩረት በመስጠት ነቅተን ለመጠበቅና እርስ በእርስ ለሚደጋገፉ እንዲሁም ሰላማችንን ማረጋገጥ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ጏላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት አባላት ከመደበኛው የፀጥታ መዋቅር ጋር ተቀናጅተው በመስራት አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅሰው የሰላምና ደህንነት ተግባራችን እንደሁልጊዜው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል::

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች