image
image
image
image
image

ህዝቡ እራሱ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ የሰላምና ደህንነት ስራ መሰራቱ ተገለፀ::

ሀምሌ 1, 2017
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በዓት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድን ከፀጥታ ሃይሎች፣ ከሰላም ሰራዊት አባላት እና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር አወያይተዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ መስቀል፣ ኢሬቻና መውሊድ አይነት ታላላቅ የአደባባይ በዓላትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የተቀናጀና ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የሰላምን ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ ሻምበል ኡባድ ጁና በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ህግና ስርዓት እንዲከበር እንዲሁም ህገወጥነትን በመከላከል አበረታች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል:: የውይይቱ ተሳተፊ የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው ‎የሰላም ምንጭም የሰላም ዘብም ህብረተሰቡ በመሆኑ ለሰላማችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል:: ‎

መልዕክትዎን ይላኩ