image
image
image
image
image

ለግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፣ ለኮንዶሚኒየምና ለማህበር ቤት ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ታህሳስ 11, 2017
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ለፌዴራል ፓሊስ አባላት፣ ለግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፣ ለቅጥር ጥበቃ አባላት፣ ለኮንዶሚኒየምና ለማህበር ቤቶች ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ሲስጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀዋል። መድረኩን የመሩት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ በመከላከል በዜጎችና ሀገር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የሁሉንም የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቅርበት ከህብረተሰቡ ጋር ለመሥራት የተለያዩ የኤጀንሲዎችንና የተቋማትን ንብረት ከስርቆት ለመጠበቅ ሲባል የወንጀል መከላከል ስትራቴጂውን የማስገንዘብና በወንጀል መከላከል ስራ ከህብረተሰቡ ጋር እንዴት በጋራ እንደሚሰራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታላሚ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፓሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ኮማንዶር ተስፋዬ ደገፋ በበኩላቸው የወንጀል መከላከል ፈፃሚዎች አቅም ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም መስፈን ጠንካራ የፍትሕ ስርዓት እንደሚረጋገጥ እና በወንጀል መከላከል ውስጥ ህብረተሰቡን ካልያዝን ወንጀል መከላከላችን ውጤታማ አይሆንም ሲሉ ባቀረቡት ሰነድ ገልጸዋል ። በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ጽ/ቤት የግል ጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ቁጥጥርና ፈቃድ ከፍተኛ ባለሙያ ኢንስፔክተር ሙሉጌታ ገላው በበኩላቸው ለፌዴራል ፓሊስ አባላት፣ የቅጥር ጥበቃና ለግልና ለተቋማት ጥበቃዎች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ወንጀልን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም አስቀድሞ በመከላከል የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ እንደሚቻልና የተቋማትን ሰላም፣ ደኅንነትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ መቻሉ ሥራዎችን ስልታዊና ቴክኒካል ባለው እውቀትና ክህሎት እንዲመራና ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ይረዳናል ሲሉ በማስገንዘብ የእለቱ የስልጠና መድረክ ተቋጭቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች