image
image
image
image
image

በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።

ሀምሌ 4, 2017
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከሃይማኖት አባቶች ፣ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ከአባገዳ፣ ከነጋዴው ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሄደ ። መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዳሉት የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ኃላፊነትና ተግባር እንደመሆኑ መጠን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን ብሎም የክፍለ ከተማችንን የሰላም ደህንነት በአስተማማኝ የፀጥታ ሥራዎች በጋራ የሚሠራ መሆኑን ገልፀው ፣ በቀጣይ የሠላም ሠራዊትን አቅምና ግብዓት በማማሟላት ጠንካራ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች መሥራት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የፀጥታ መረጃ ቅጥር ማደራጃና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን አቶ ዮሐንስ ወልዴ በበኩላቸው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የመልካም አስተዳደር ሥራዎችና የ90 ቀናት እቅድ ሰነድ ለተሳታፊዎች በዝርዝር አቅርበዋል። የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፀጥታ ሥራዎችን የምንሠራው የአከባቢያችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና መወጣት ይገባናል ሲሉ ገለፀወል። ‎

መልዕክትዎን ይላኩ