image
image
image
image
image

የአካባቢን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሰላም ሠራዊት አባላት አይተኬ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ::

ታህሳስ 22, 2017
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከሁሉም ወረዳ አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት በሰላምና ፀጥታ ትግበራ ዙሪያ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል:: የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የክፍለ ከተማችንን ሠላምና ፀጥታ ለማስፈን የሠላም ሠራዊት አይተኬ ሚና እንዳላቸው ባለፉት ሥራ ላይ በነበሩት የሠላም ሠራዊት ሁሉ አቀፍ የሠላምና ፀጥታ ሥራዎችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቁርና ፀሐይ ሳይበግራቸው ሲሰሩ ቆይተዋል፤ በመሆኑም ዛሬ የሚሰጠውን የሠላም ሠራዊት ንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና በትኩረት በመከታተል ሰልጥናችሁ ለአካባቢያችን የተረጋጋና ከተለያዩ የወንጀል ድርጊት የፀዳ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባችኋል ሲሉ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው ክፍለ ከተማው የሀገራች ትልቁ የክፍት ገበያ መርካቶ መገኛ እና የሀገራችን የንግድ ማቀላጠፊያ የጀርባ አጥንት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን የገበያ እንቅስቃሴውን ሰላማዊና የተረጋጋ ለማድረግና ሌሎችንም የፀጥታ ሥራዎችን ከመደበኛ የፀጥታ አካላት በተጨማሪ የሠላም ሠራዊት ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ከሁሉም ወረዳ አዲስ ለተመለመሉ የሠላም ሠራዊት በሰላምና ፀጥታ ትግበራን አስመልክቶ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና በተጨማሪ በቀጣይ ባሉት ቀናት የአካል ብቃት፣ የስነ ልቦና ቁርጠኝነት እንዲሁም ጥብቅ የሠላም ሠራዊት ዲሲፕሊን ሥነ ምግግ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ የወንጀል መከላከልና ማህበረሰብ አቀፍ ኃላፊ ዋና እንስፔክር ጳውሎስ ተመስገን በበኩላቸው ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል በእንቅስቃሴ ውስጥ የማስተወል ጥበብንና ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ እንደሚቻልና የአካባቢን ሰላም፣ ደኅንነትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል። የጽ/ቤቱ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አምባዬ ወ/ማርያም በበኩላቸው 6ኛ ኮርስ ለአዲስ የሠላም ሠራዊት ተመልማይ የንድፈ ሀሳብና የክህሎት ስልጠና እንዲሁም በሠላም ሠራዊት መተዳደሪያ ደንብ የተዘጋጁ ሰነዶችን በዝርዝርና በስፋት አቅርበዋል። ከላይ ከተጠቀሱት ኃላፊዎች በተጨማሪ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መመሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር መኮነን አሻግሬና የፖሊስ ባልደረቦቹ እና የወረዳ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች