በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ዝርዝር አገልግሎቶች
- ከፀጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎች መቀበልና ምላሽ መስጠት
- 2. ለጦር መሳሪያ አጠቃቀምና አያያዝ ፍቃድ አስተዳደራዊ ድጋፍ መስጠት
- 3. የፀጥታ መረጃ አገልግሎት፣
- የፀጥታ መረጃና ጥቆማ መቀበል፣ ማጣራት እና ምላሽ መስጠት ፣
- የ24 ሰዓት መረጃ መሰብሰብ መተንተን
- 4. የኃይማኖት ተቋማት የመመዝገብ አገልግሎት፣
- 5. ከኃይማኖት ተቋማት ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
- በተመሳሳይና በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለ የቦታ ርቀት ላይ ለሚነሳ ቅሬታ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት ፣
- በሃይማኖት ተቋም ውስጥ የሚነሱ የውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ የመስጠት አገልግሎት ፣
- ባልተፈቀደ ቦታ ላይ የሃይማኖት አስተምህሮት እና ፀሎት ስነ ስርዓት በሚፈፀሙ ተቋማት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ የመስጠት አገልግሎት ፣
- በመኖሬያ አካባቢ የሚፈጠሩ የድምጽ ብክለት ችግር ምላሽ የመስጠት አገልግሎት ፣
- 6. አዲስ የኃይማኖት ተቋማት ለሚመሰረቱ አካላት የሰላማዊነት ማረጋገጫ የመስጠት አገልግሎት፤
- 7. ለብዙሃን ማህበራት እና አደረጃጀቶች የምዝገባና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፤