የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ወለል
+251911393087
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የዜጎች ስምምነት ሰነድ
ተቋማዊ አደረጃጀት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች
የደንበኞች አገልግሎት
ዋና ዋና አገልግሎቶች
የጸጥታ መረጃ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ስራዎች
የሰላም እሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ስራዎች
የጸጥታ ጉዳዮች ክትትል ቁጥጥር እና ኦፕሬሽን ስራዎች
የህብረተሰብ አደረጃጀት ተሳትፎ እና የብዙሃን ማህበራት ድ/ክትትል ሥራዎች
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
መጽሄቶች | Magazines
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
የዶ/ር ዐቢይ መጽሀፍቶች
ብሮሸር | Brochure
በራሪ ወረቀት
ማስታወቂያ
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
ህዝቡ እራሱ የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን በማድረግ ውጤታማ የሰላምና ደህንነት ስራ መሰራቱ ተገለፀ::
ሀምሌ 1, 2018
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በዓት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድን ከፀጥታ ሃይሎች፣ ከሰላም ሰራዊት አባላት እና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር አወያይተዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንደ መስቀል፣ ኢሬቻና መውሊድ አይነት ታላላቅ የአደባባይ በዓላትን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የተቀናጀና ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የሰላምን ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ ሻምበል ኡባድ ጁና በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ህግና ስርዓት እንዲከበር እንዲሁም ህገወጥነትን በመከላከል አበረታች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል:: የውይይቱ ተሳተፊ የሰላም ሰራዊት አባላት በበኩላቸው የሰላም ምንጭም የሰላም ዘብም ህብረተሰቡ በመሆኑ ለሰላማችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተን መስራታችንን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል::
ዜና | Oduu | News
ህጋዊ የደረሰኝ ግብይት በማስፈን የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ሀምሌ 2, 2018
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የገበያ ማረጋጋት የጋራ ግብረ-ሃይል የተረጋጋ ገበያ ከመፍጠር አንፃር እንዲሁም ከደረሰኝ ቁጥጥር እና ክትትል ጋር እየተሰራ ያለውን ስራ ገምግሟል:: በመድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልዋሂድ በድሩ፣ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዲሁም ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል:: የደረሰኝ ቁጥጥርና ክትትል ስራውን በማጠናከር ህጋዊ ግብይት ማስፈን እንደሚገባ የገለፁት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዜና | Oduu | News
በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
ሀምሌ 4, 2018
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተሠሩ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከሃይማኖት አባቶች ፣ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ከአባገዳ፣ ከነጋዴው ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሄደ ። መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዳሉት የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ኃላፊነትና ተግባር እንደመሆኑ መጠን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን ብሎም የክፍለ ከተማችንን የሰላም ደህንነት በአስተማማኝ የፀጥታ ሥራዎች በጋራ የሚሠራ መሆኑን ገልፀው ፣ በቀጣይ የሠላም ሠራዊትን አቅምና ግብዓት በማማሟላት ጠንካራ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች መሥራት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ። በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የፀጥታ መረጃ ቅጥር ማደራጃና ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን አቶ ዮሐንስ ወልዴ በበኩላቸው የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የመልካም አስተዳደር ሥራዎችና የ90 ቀናት እቅድ ሰነድ ለተሳታፊዎች በዝርዝር አቅርበዋል። የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፀጥታ ሥራዎችን የምንሠራው የአከባቢያችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና መወጣት ይገባናል ሲሉ ገለፀወል።
ዜና | Oduu | News
የሰላም ሠራዊትን ማጠናከር አስፈላጊ መኾኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ሀምሌ 4, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምላሻቸው የሰላም እና ደኅንነት ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን ገልጸዋል። አሁንም የዝርፊያ እና የጸረ ሰላም ኀይሎች እንቅስቃሴ እንዳለ ተናግረዋል። ሕዝቡ የሰላሙ ዋነኛ ባለቤት በመኾኑ የሰላም ሠራዊቱን በቁጥር፣ በጥራት እና በብቃትም ማጠናከር አስፈላጊ መኾኑን አስገንዝበዋል። ከተማዋ የወንጀለኞች መሸሸጊያ እንዳትኾን ዘመናዊ የሴኩሪቲ መሳሪያዎች መትከል እና በሕዝብ እና በጸጥታ ኀይሎች መካከል ያለውን ቅንጅት ማሳደግ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል። በተሠራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበበት አብራርተዋል። ይህ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል። የመሬት ልማት አሥተዳደር አገልግሎቶችን ፈጣን እና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎት ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ መኾናቸውንም ጠቁመዋል። አሁን ባለው ደረጃ 347 አገልግሎቶችን በ"መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት" ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። በቀጣይም የዕውቀት እና ልምድ ልውውጥን በማስፋት ዲጂታል አገልግሎቱን ለማሻሻል እንደሚሠራ ነው ያስገነዘቡት። ከ4ሺህ በላይ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሌብነት እና በሙስና ወንጀል ተሰማርተው በመገኘታቸው ሕግ የማስከበር ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል። ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንቲባዋ አስታውቀዋል። አገልጋይ ማገልገል ግዴታው፣ ተገልጋይም መገልገል መብቱ በመኾኑ ሙስናን መዋጋት ተገቢ እንደኾነም አጽንኦት ሰጥተዋል። የነዋሪዎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ በተሠራው ሥራ ከ55 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት እንዳደረጉ ከንቲባዋ ገልጸዋል። በቀጣይ በጀት ዓመት የቤት ግንባታ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ እና መንግሥት ብቻውን መመለስ ስለማይችል ባለሃብቶችን በመሬት አቅርቦት እና ድጋፍ በመስጠት በቅንጅት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። የኑሮ ውድነትን ለመግታት እና ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረትን ለመከላከል የከተማ አሥተዳደሩ በድጎማ፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ በገበያ ማዕከላት እና በእሑድ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በማቅረብ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የኑሮ ጫና እንዳይበረታ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ይህ ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስገነዘቡት። ጉባኤው በከሰዓት ውሎው የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦለት ውይይት አድርጎበታል። በነገ ውሎው ደግሞ የዳኞችን፣ የተለያዩ ሹመቶችን እና በአዲስ የሚቋቋሙ ተቋማትን በአዋጅ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ዘጋቢ፦ አዲሱ ዳዊት የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ
ዜና | Oduu | News
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረሃይል በወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ግምገማ አካሄደ፡፡
ሀምሌ 8, 2018
በመድረኩ የጋራ ግብረሃይሉ አባላት፣ የፖሊስ መምሪያ የስራ ሃላፊዎችና የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተገምግመዋል፡፡ የውይይት መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ስራ መሰራቱ ውጤት እየተገኘበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ገልፀዋል:: የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በበኩላቸው ህዝቡን የሰላሙ ባለቤት አድርጎ መስራት ተገቢ መሆኑን ገልፀው የየወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የተቀናጀ ስምሪት በመውሰድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል:: የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብነት አሰግድ በበኩላቸው ለሰላምና ፀጥታ ተግራራችን ልዩ ትኩረት በመስጠት ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል:: የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል::
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
የዛሬይቱ ልደታ
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ያግኙን
addiskps@gmail.com
+251911393087