image
image
image
image
image

በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የሚገኙ የሰላም ክበባት ለመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።

ህዳር 21, 2017
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከመንግስትና ከግል ት/ቤቶች ለተውጣጡ የሰላም ክበባት አመራሮች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሳለጥ ሚናቸውን እንዲወጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሂዷል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ት/ቤቶች ውስጥ የሰላም ክበባት አደረጃጀትን በማጠናከር ሰላምን የማስረፅ እና የሰላም ክበባት የትምህርት ቤት ውስጣዊና ውጫዊ አዋኪ ድርጊቶችንና የቡድን ግጭትን በማስወገድ የመማር የማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ የማድረግ እንዲሁም ተማሪዎችን በስነ-ምግባር ለማነፅ የሚያስችል የተቀናጀ ሥራ በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የህብረተሰብ አደረጃጀትና ተሣትፎ ሥራዎች አስተባባሪ አቶ አምባዬ ወ/ማርያም በበኩላቸው የሰላምን አስፈላጊነትና የተማሪዎች ስነ-ምግባርና የትምህርት ቤቶች የሰላም ክበባት አባላትና መምህራንን ጨምሮ በክበባቱ አባላት የሚሰጡት ጥቆማ አማካኝነት አዋኪ ድርጊቶች እና የቡድን ግጭት ዙሪያ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ከስጋት ነፃ የማድረግ ኃላፊነትና ተግባር መወጣት ይገባችኋል ሲሉ ባዘጋጁት የስልጠና ሰነድ በዝርዝር አቅርበዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሰላም ክበባት አባላት ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚገኙ አዋኪ ድርጊቶችን በመከታተል መጠቆም ፣ በባህሪ ወጣ ያሉ ተማሪዎችን የመምከር ሥራና በሰላማዊ የመማር የማስተማር ሂደት ዙርያ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራታቸውን ገልጸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች