image
image
image
image
image

በአዲስ ከተማ ከ/ከተማ የሰባተኛ ኮርስ ዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላት ስልጠና የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

መጋቢት 11, 2017
በክፍለ ከተማው ከሁሉም ወረዳ ለተመለመሉ ዕጩ የሠላም ሰራዊት "24 ሰዓት የማይተኛ፤ ለከተማችን ሰላምና ብልፅግና የሚተጋ!!" በሚል መሪ ሀሳብ የ7ኛ ኮርስ የሠላም ሰራዊት የንድፍ ሀሳብ ስልጠና ለ10 ተከታታይ ቀናት በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል። መድረኩን የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው አስከአሁን በመጣንባቸው ጊዜያት እጅግ አመርቂ የሰላምና ፀጥታ ተግባራት መከናወናቸውን እና በንቁ የሠላም ሰራዊትና የህዝብ ተሳትፎ ውጤታማ ሥራ እንደተሰራ፣ የልማት ሥራዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሰረቱ ሰላምን በማስፈን በመሆኑ በጠንካራ የሰላም ሠራዊት የፀጥታ ስራዎችን ለማከናወን የ7ኛ ኮርስ የሠላም ሰራዊት የንድፍ ሀሳብ ስልጠና ለ10 ተከታታይ ቀናት በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚሰጥ መሆኑን አሳስበዋል። የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የክፍለ ከተማችን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝነት ጠብቆ ለማቆየት ሁለንተናዊ ተሳትፎን በማስፋት ከሁሉም የፀጥታ አደረጃጀትና አካላት ጋር በንቃት የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል። የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው ለምልምል የሠላም ሠራዊት የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሰነድ በስፋትና በዝርዝር አቅረበዋል። በተመሳሳይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላት ስልጠና ለ10 ቀናት በንድፈ ሃሳብና በመስክ ወታደራዊ የተግባር ልምምድ የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች