Welcome to >Addis Ketema Peace and Security Office!       እንኳን ወደ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ ክ/ከተማችን በህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት፤ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለኑሮ፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ እንድትሆን ይተጋል!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በከተማው አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 74/2014 በከተማዋ ዘላቂና አስተመማማኝ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የማረጋገጥና ተልዕኮ ተሰጥቶት የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣትና ያስቀመጠውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በየጊዜው አዳዲስ አሠራሮችንና የለውጥ መሳሪያዎችን በስራ ላይ በማዋል ከጊዜ ወደ ጊዜ በመዋቅሩ ላይም ሆነ በአሰራርና በአመለካከት ላይ ለውጦች እንዲመዘገቡ ጥረቶች ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

በዚህም የተቋሙ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉትን አሠራርና አደረጃጀቶች እንደገና በማጤን አገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን በሰው ሀይልና በግብዓት አቅርቦት የተሟላ በማድረግና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በተቀናጀና በተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ሴክተሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት ሴክተሩ ከተቋቋመለት ዓላማ አንፃር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና የሰላም ባለቤትነት ለማረጋገጥ በተለይም ህዝቡ የዚህ ዓላማ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን በሚደረገው ...... ተጨማሪ ያንብቡ

ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ , የአዲስ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች:-

የጽ/ቤቱ አስተባባሪዎች

አቶ በላይነህ ታደለ

የጸጥታ መረጃ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ስራዎች አስተባባሪ

ፀሀይ ሃይሌ

የሰላም እሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ስራዎች አስተባባሪ

ኮማንደር ሽመልስ ባልቻ

የጸጥታ ጉዳዮች ክትትል ቁጥጥር እና ኦፕሬሽን ስራዎች አስተባባሪ አስተባባሪ

አምባዬ ወ/ማሪያም

የህብረተሰብ አደረጃጀት ተሳትፎ እና የብዙሃን ማህበራት ድ/ክትትል ሥራዎች አስተባባሪ

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡