የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በከተማው አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 74/2014 በከተማዋ ዘላቂና አስተመማማኝ ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን የማረጋገጥና ተልዕኮ ተሰጥቶት የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣትና ያስቀመጠውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት በየጊዜው አዳዲስ አሠራሮችንና የለውጥ መሳሪያዎችን በስራ ላይ በማዋል ከጊዜ ወደ ጊዜ በመዋቅሩ ላይም ሆነ በአሰራርና በአመለካከት ላይ ለውጦች እንዲመዘገቡ ጥረቶች ሲያደረግ ቆይቷል፡፡ በዚህም የተቋሙ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉትን አሠራርና አደረጃጀቶች እንደገና በማጤን አገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ የተቀላጠፈ እንዲሆን በሰው ሀይልና በግብዓት አቅርቦት የተሟላ በማድረግና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በተቀናጀና በተደራጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ደረጃ በደረጃ በመቅረፍ ሴክተሩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡
በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት ሴክተሩ ከተቋቋመለት ዓላማ አንፃር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና የሰላም ባለቤትነት ለማረጋገጥ በተለይም ህዝቡ የዚህ ዓላማ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅሰቃሴዎች ውሰጥ የማይተካ ሚና አለው ፡፡
በዚህ መሰረት ሴክተሩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ፣የአገልግሎት ስታንዳርዶች፣ ተገልጋዩ ማሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታዎች እና አገልግሎቱ የሚሰጥበትን የስራ ክፍል በማካተት የዜጎች የስምምነት ሰነድ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ይህ የ2017 በጀት ዓመት የዜጎች ሰምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል ፡፡
የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ
-
ሴክተሩ የሚሰጠው አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ተደራሽ፣ ፍትሀዊና ግልፅ በማድረግ በተጨማሪም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ተገልጋዩ ጠያቂ እንዲሆን በማስቻል የልማትና የመልካም አስተዳደር ስርዓት ቀጣይነትን ማረጋገጥ የቻርተሩ ዓላማ ይሆናል፡፡፣
- አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣
- በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች
የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Mission and Vision ይጫኑ
የተገልጋዮች መብት
- መ/ቤቱ ባስቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የመስተናገድ፣
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታን የመግለጽና አስተያየት የማቅረብ፣
- ስለመ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ አስፈላጊውን እና ማግኘት የሚገባቸውን መረጃ የማግኘት፣
- የመ/ቤቱን የዕቅድ አፈፃፀም ማወቅ ተሳትፎ በማድረግ ማጎልበት፣
- መብትን በአግባቡ የመጠየቅ፣
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታን የመግለጽና አስተያየት የማቅረብ፣ ፈጣን ምላሽ የማግኘት፣
- ተገልጋዮች አገልግሎቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቻው፡፡
- 9 ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት፣ አላቸው።
የተገልጋዮች ግዴታዎች
- አላስፈላጊና ከሥነ-ምግባር ውጪ የሆኑ ባህሪያትን ከማሳየት መቆጠብ፣
- ጥያቄዎችን በግልፅና እንደ አስፈላጊነቱ በህጋዊ ማስረጃዎችና ሰነዶች በማስደገፍ ማቅረብ፣
- አገልግሎቶችን ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት፣
- የመሥሪያ ቤቱን ሕግና ሥርዓት የማክበር፣
- ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ፤
- በአገልግሎት አሰጣጡ ቅር የተሰኘ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓትን በመከተል ቅሬታን ለሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው ማቅረብ፣
ተቋሟዊ አደረጃጀት